ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዮናስ 2:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

2. እንዲህም አለ፤“ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤እርሱም መለሰልኝ፤ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤አንተም ጩኸቴን ሰማህ።

3. ጥልቅ ወደ ሆነው፣ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣በላዬ አለፉ።

4. እኔም፣ ‘ከፊትህ ጠፋሁ፣ነገር ግን እንደ ገና፣ወደ ቅዱስ መቅደስህ፣እመለከታለሁ’ አልሁ።

5. ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ፤ጥልቁም ከበበኝ፤የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ።

6. ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤አንተ ግን ሕይወቴን ከጒድጓድ አወጣህ።

7. “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ጸሎቴም ወደ አንተ፣ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዮናስ 2