እግዚአብሔር (ያህዌ) ከብርቱ ቊጣው ይመለስ ዘንድ እርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል፤