ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤“የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋር እሆናለሁ።