የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ሥብ ጠግባለች፤በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቶአልና።