በደቡብ በኩል ያሉት ክፍሎች በሮች መጠናቸው ተመሳሳይ ነበር። ከመመላለሻው መነሻ ላይ መግቢያ በር አለ፤ መመለሻውም ፊት ለፊት ካለው ወደ ምሥራቅ ከሚያመራው ግንብ ጋር ተጓዳኝ ነው።