ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።