ምዕራፎች

 1. 1
 2. 2
 3. 3
 4. 4
 5. 5
 6. 6
 7. 7
 8. 8
 9. 9
 10. 10
 11. 11
 12. 12
 13. 13

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 1 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ልጁ ከመላእክት በላይ ነው

1. እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ፣

2. በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን።

3. እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራ ቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።

4. ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኖአል።

5. እግዚአብሔር፣“አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤”ወይስ ደግሞ፣“እኔ አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?

6. ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣“የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል።

7. ስለ መላእክትም ሲናገር፣“መላእክቱን ነፋሳት፣አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል።

8. ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤

9. ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣የደስታንም ዘይት ቀባህ።”

10. ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተበመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

11. እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

12. እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”

13. እግዚአብሔር፣“ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?

14. መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?