ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ውድሽ ወዴት ሄደ?አብረንሽም እንድንፈልገው፣ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?

2. ውዴ መንጋውን ለማሰማራት፣ውብ አበቦችንም ለመሰብሰብ፣የቅመማ ቅመም መደቦቹ ወዳሉበት፣ወደ አትክልት ቦታው ወርዶአል።

3. እኔ የውዴ ነኝ፤ ውዴም የእኔ ነው፤መንጋውንም በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል።

4. ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።

5. አስጨንቀውኛልና፣እባክሽ ዐይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ፤ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ የሚወርድ፣የፍየል መንጋ ይመስላል።

6. ጥርሶችሽከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።

7. ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

8. ሥልሳ ንግሥቶች፣ሰማንያ ቁባቶች፣ቊጥራቸውም የበዛ ደናግል ሊኖሩ ይችላሉ፤

9. እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፤ለእናቷም አንዲት ናት፤ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ”አሏት፤ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት።

10. እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?

11. በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀሉትን አትክልቶች ለማየት፣ወይኑ ማቈጥቈጡን፣ሮማኑ ማበቡን ለመመልከት፣ወደ ለውዙ ተክል ቦታ ወረድሁ።

12. ይህን ከማወቄ በፊት፣ምኞቴ በሕዝቤ ንጉሣዊ ሠረገሎች መካከል አስቀመጠኝ።