ምዕራፎች

 1. 1
 2. 2
 3. 3
 4. 4
 5. 5
 6. 6
 7. 7
 8. 8
 9. 9
 10. 10
 11. 11
 12. 12
 13. 13
 14. 14

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሆሴዕ ከሚስቱ ጋር መታረቅ

1. እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “እርሷ በሌላ ሰው የምትወደድ አመንዝራ ብትሆንም፣ አሁንም ሂድና ሚስትህን ውደዳት፤ ወደ ሌሎች አማልክት ዘወር ቢሉና ለእነርሱም የተቀደሰውን የዘቢብ ጥፍጥፍ ቢወዱም፣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንደ ወደዳቸው አንተም እርሷን ውደዳት።”

2. ስለዚህ በዐሥራ አምስት ሰቅል ጥሬ ብርና በአንድ ቆሮስ ተኩል መስፈሪያ ገብስ ገዛኋት።

3. እኔም፣ “ከእኔ ጋር ብዙ ቀን ተቀመጪ፤ አታመንዝሪ ወይም ሌላ ሰው አትውደጂ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” ብዬ ነገርኋት።

4. እስራኤላውያን ለብዙ ዘመን ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፣ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዐምደ ጣዖት፣ ያለ ኤፉድና ያለ ጣዖት ምስል ይኖራሉና።

5. ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።